ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ አሁን ላይ እዳዋን ለመክፈል ምንም ችግር የለባትም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ አሁን ላይ እዳዋን ለመክፈል ምንም ችግር የለባትም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የእዳ ሽግሽግን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ እና ማብራሪያ ኢትዮጵያ አሁን ላይ እዳዋን ለመክፈል ምንም ችግር የለባትም ብለዋል።

በሪፎርሙ አማካኝነት ከ4 አስከ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የእዳ ሽግሽግ ተደርጓል ነው ያሉት።

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎም መንግስት አንድም ዶላር የንግድ ብድር አልወሰደም ሲሉም አክለዋል።

ይህም እዳን ለመቆጣጠር ያለንን ጽኑ አቋም ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም