አመራሩ የህብረተሰብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
አመራሩ የህብረተሰብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
ቦንጋ፤ ጥቅምት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አመራሩ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) አስገነዘቡ ።
በክልሉ የመንግስትና የፓርቲ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።
ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንደገለፁት አመራሩ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራት እንዲጠናከሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል ።
ተግባራትን በዕቅድ በመምራትና በውጤት መለካትን ባህል ማድረግ እንደሚገባውም አስገንዝበዋል።
በተለይም በንቅናቄ የሚመሩ የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማት ስራዎችን በጥራትና በስፋት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በቀጣይ ሞዴል መንደሮችን መፍጠር ላይ ትኩረት እንደሚደረግም አመላክተዋል።
ከተረጂነት በመላቀቅ በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከርና አገልግሎት አሰጣጥን ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራ በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በበኩላቸው ውጤታማ አመራር በመፍጠር የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ላይ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል።
በመድረኩ የክልልና የዞን አመራሮች ተሳትፈዋል።