ሐረማያ ዩኒቨርስቲ 5ሺ 435 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ሐረማያ ዩኒቨርስቲ 5ሺ 435 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው
ሐረማያ፤ ጥቅምት 17/2018 (ኢዜአ)፡- ሐረማያ ዩኒቨርስቲ 5ሺ 435 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው ።
የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት አባላትና ነባር ተማሪዎች በመቀናጀት ለተማሪዎቹ አቀባበል እያደረጉ ነው ።
በቅበላ መርሐ ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
የዩኒቨርስቲው የአንደኛ አመት ተማሪዎች ፕሮግራም ዳይሬክተር ጌታቸው ተሾመ (ዶ/ር) እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው የተመደቡለትን 5 ሺህ 435 የመጀመሪያ አመት ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።
ዩኒቨርሲቲው በአዲስአበባ፣ አዳማ፣ ደንገጎና ሃረማያ ከተማ የተማሪ ህብረት አስተባባሪዎችን በመላክ ጭምር አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በመቀበል ወደ ዩኒቨርሲቲው እንዲደርሱ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን ተቀብሎ የመማር ማስተማር ሥራውን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ የመኝታ፣የመማሪያና የመመገቢያ ክፍሎች እንዲሁም የመማርያ ቁሳቁስ ዝግጅት ማድረጉን አመልክተዋል።
በዩኒቨርስቲው የተመደቡት ተማሪ ሲቱናፍ ተመስገንና ተማሪ ዋቅጅራ አማኑኤል እንደገለፁት፤በአካባቢው ማህበረሰብና ነባር ተማሪዎች በተደረገላቸው የደመቀ አቀባበል መደሰታቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይም ለትምህርታቸው ትኩረት ሰጥተው የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደሚተጉ አክለዋል።