ሊቨርፑል በሊጉ አራተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናገደ - ኢዜአ አማርኛ
ሊቨርፑል በሊጉ አራተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናገደ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት መርሃ ግብር ብሬንትፎርድ ሊቨርፑልን 3 ለ 2 አሸንፏል።
ማምሻውን በጂቴክ ኮሙኒቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዳንጎ ኡታራ እና ኬቨን ሻደ በጨዋታ፣ ኢጎር ቲያጎ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሚሎስ ኬርኬዥ እና መሐመድ ሳላህ ለሊቨርፑል ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል አራተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል። ቀያዮቹ በ15 ነጥብ ወደ ስድስተኛ ደረጃ ዝቅ ብለዋል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው ብሬንትፎርድ በ13 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።