ቀጥታ፡

ማንችስተር ዩናይትድ በሊጉ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት መርሃ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ብራይተንን 4 ለ 2 አሸንፏል።

ማምሻውን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብሪያን ምቡዌሞ  ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ማቲያስ ኩንሃ እና ካሲሚሮ ቀሪዎቹን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ዳኒ ዌልቤክ እና ቻራላምፖስ ኮስቱላስ ለብራይተን ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ዩናይትድ በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ስር በሊጉ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል። በ16 ነጥብ ደረጃውን ወደ 4ኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ብራይተን በ12 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም