በፕሪሚየር ሊጉ ሰንደርላንድ ቼልሲን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ ሰንደርላንድ ቼልሲን አሸነፈ
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 15/ 2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሰንደርላንድ ቼልሲን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በስታምፎርድ ብሪጅ በተካሄደው ጨዋታ አሊሃንድሮ ጋርናቾ በአራተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ቼልሲን መሪ አድርጋለች።
ዊልሰን ኢሲዶር በ22ኛው እና ቼምስዳይን ታልቢ በ91ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፏቸው ጎሎች ሰንደርላንድ አሸናፊ ሆኗል።
ጨዋታውን ተከትሎ ሰንደርላንድ በ17 ነጥብ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ ሲያደርግ ፣ ቼልሲ በ14 ነጥብ ወደ ሰባተኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል።
በሌላኛው ጨዋታ ኒውካስትል ዩናይትድ ፉልሃምን 2 ለ 1 አሸንፏል። ጃኮብ መርፊ እና ብሩኖ ጉማራይሽ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሳሳ ሉኪች ለፉልሃም ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።