ሲዳማ ቡና የሊጉ መሪ የሆነበትን ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ሲዳማ ቡና የሊጉ መሪ የሆነበትን ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 15/ 2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሲዳማ ቡና ሃዋሳ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ያሬድ ባየህ በ52ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ድሉን በማስመዝገብ በስድስት ነጥብ ሊጉን መምራት ጀምሯል።
በአንጻሩ ሃዋሳ ከተማ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
ጨዋታውን ተከትሎ የሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል። የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳሉ።