የግብርናው ዕድገትም በአርሶና አርብቶ አደሩ ኑሮ ሁሉ የሚገለጥ ሆኗል - ሚኒስትር አዲሱ አረጋ - ኢዜአ አማርኛ
የግብርናው ዕድገትም በአርሶና አርብቶ አደሩ ኑሮ ሁሉ የሚገለጥ ሆኗል - ሚኒስትር አዲሱ አረጋ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ)፦ የግብርናው ዕድገትም በአርሶና አርብቶ አደሩ ኑሮ ሁሉ የሚገለጥ ሆኗል ሲሉ የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ ገልጸዋል።
የግብርናው ዕድገት ከሌሎች ዘርፎች ዕድገት ጋር ተሳስሮ በመሠራቱ ተስፋችንን መጨበጥ ጀምረናል ሲሉም ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ ከሚኒስትሮች ጋር በመሆን በኮይሻ ግድብ አካሂደዋል።
በዚህ ወቅት የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ እንደተናገሩት የግብርናው ዕድገትም በአርሶና አርብቶ አደሩ ኑሮ ሁሉ የሚገለጥ ሆኗል ብለዋል።
ከ100 ቀናት አፈጻጸም ጋር በተያያዘም በሁሉም መስኮች ተስፋ የሚፈነጥቁ አፈጻጸሞች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም እንደ ሀገር የተሻለ ስራ መሰራቱን የሚያሳይና የኮይሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ የፕሮጀክት ቅልጥፍና ውጤታማነት የታየበት ነው ብለዋል፡፡
የሕዳሴው ግድብ፣ የወልመል መስኖ፣ የማዳበሪ ፋብሪካ እና ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶች ተስፋችንን መጨበጥ መጀመራችንን ብሎም የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬነት አመላካች ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።
አፈጻጸሙ እንደሚያስረዳው የተቀመጡ ግቦች በስኬት እየተከናወኑ ነው፤ የግብርናው ዕድገትም በአርሶና አርብቶ አደሩ ኑሮ ሁሉ የሚገለጥ ሆኗል ነው ያሉት።
የተመዘገቡት ውጤቶች የተገኙት በፈተና ውስጥ መሆኑ ደግሞ ሀገራችንን ፈተና ሳይበግራት ስኬታማ ጉዞ ማድረግ መቻሏን እንደሚያሳይ አንስተዋል።
አዲስ የሥራ ባህል እየተፈጠረ መሆኑን ዐይቻለሁ ያሉት ሚኒስትሩ፤ ሕዝብን በማሳተፍ ጀምሮ የመጨረስ ዐቅም እያደገ መምጣቱንም ታዝቤያለሁ ብለዋል።