የኮይሻ ግድብ የኢትዮጵያን አቅም በተግባር የገለጠ ፕሮጀክት ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኮይሻ ግድብ የኢትዮጵያን አቅም በተግባር የገለጠ ፕሮጀክት ነው
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018 (ኢዜአ):- የኮይሻ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክት የኢትዮጵያን አቅም በተግባር የገለጠ ፕሮጀክት መሆኑን የፍትህ ሚኒስትር ሀና አርዓያሥላሴ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2018 ዓመተ ምህረት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ አስመልክቶ በኮይሻ ግድብ ከሚኒስትሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።
የፍትህ ሚኒስትር ሀና አርዓያሥላሴ በውይይቱ ወቅት የኮይሻ ግድብ ዘላቂ የኢነርጂ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ እና የአመራር ቁርጠኝነት በግልጽ የሚያሳይ እና የኢትዮጵያን አቅም በተግባር የገለጠ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለግንባታው የሰጡትን በሳል አመራር እና አካሄድ አድንቀዋል።
ህዳሴ ግድብ፣ ኮይሻ ግድብ እና ሌሎች ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያ ኩራት ምንጭ እና ትውልድ የሚሻገሩ ስራዎች መሆናቸውን አመልክተዋል።
በፕሮጀክቶቱ የኢትዮጵያውያንን የመፈጸም አቅም እና የእውቀት ሽግግር እድገት የታየበት መሆኑን ተናግረዋል።