ሀገራዊ ፕሮጀክቶቹ የኢትዮጵያን እሴቶች የሚያጎሉ ናቸው - ኢዜአ አማርኛ
ሀገራዊ ፕሮጀክቶቹ የኢትዮጵያን እሴቶች የሚያጎሉ ናቸው
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018 (ኢዜአ):- የኮይሻ ግድብ እና የጨበራ ጩርጩራ ፓርክ የኢትዮጵያን እሴቶች የሚያጎሉ መሆናቸውን የባህል እና ስፖርት ሸዊት ሻንካ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2018 ዓመተ ምህረት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ አስመልክቶ በኮይሻ ግድብ ከሚኒስትሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።
የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በዚሁ ወቅት ኮይሻ እና ጨበራ ጩርጩራ ፓርክ የኢትዮጵያ ከፍታ እና የኢትዮጵያን የመዳረሻ ግብ በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል።
የሚሰሩ የልማት ስራዎች የአካባቢውን ባህል እና እሴት በመጠበቅ ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረጉ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም የኢትዮጵያን እሴቶች እንደሚያጎላ ተናግረዋል።
በለውጡ መንግስት የኢትዮጵያን ፀጋዎች በሚገባ ለይቶ በመጠቀም የሀገርን እድገት የሚያረጋግጡ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝም አመልክተዋል።