ቀጥታ፡

መሪነት ያለንን ዐውቀንና ፀጋችንን ለይተን ወደ ሀብትነት መቀየርን ይፈልጋል - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ)፦ መሪነት ያለንን ዐውቀንና ፀጋችንን ለይተን ወደ ሀብትነት መቀየርን ይፈልጋል ሲሉ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ ከሚኒስትሮች ጋር በመሆን በኮይሻ ግድብ አካሂደዋል።

ከግምገማው ጎን ለጎንም ኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ጨምሮ ጨበራ ጩርጩራ የዝሆኖች ዳና ሎጂን ጎብኝተዋል።

በዚህ ወቅት የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በሰጡት አስተያየት መሪነት ያለንን ዐውቀንና ፀጋችንን ለይተን ወደ ሀብትነት መቀየርን ይፈልጋል ብለዋል።

በሁሉም ዘርፎች እየተመዘገቡ ያሉ አፈጻጸሞች እና ስኬቶች የኢትዮጵያን ብልጽግና አይቀሬነት አመላካች መሆናቸውንም ነው የተናገሩት።

ከዚህ አንጻር ጨበራ ጩርጩራን በማልማት ወደ ሀብትነት የመቀየር ሥራ መሠራቱን ጠቅሰው፤ ይህም አካባቢውን በማስተሳሰር እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል ሲሉ ገልጸዋል።

ከፍ ሲልም በቱሪዝሙ ዘርፍ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት አመላክተው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የመሪነት ጥበብን ተጠቅመው ካለን በመጀመር መርኅ እየሠሩ መሆናቸውን ያሳያል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም