ቀጥታ፡

የኮይሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት ባለፈ ሌሎች በርካታ ትሩፋቶች ይኖሩታል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ)፦ የኮይሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት ባለፈ ሌሎች በርካታ ትሩፋቶች እንደሚኖሩት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብረሃም በላይ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ ከሚኒስትሮች ጋር በመሆን በኮይሻ ግድብ ውይይት አካሂደዋል።


 

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብረሃም በላይ(ዶ/ር) በውይይቱ ላይ በሰጡት አስተያየት፤ የኮይሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት የብልፅግና ግልጽ ራዕይ እውን የሆነበትና ነባራዊ ሁኔታ ሲመች ብቻ ሳይሆን በፈተና ውስጥም የኢትዮጵያ ብልፅግና አይቀሬነት የታየበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኮይሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከለውጡ መንግስት በፊት ስራው የቆመ ፕሮጀክት ነበር ብለዋል፡፡

የፕሮጀክቱን ስራ ማስቀጠል በማይቻልበት ሁኔታ ላይ እንደነበር በማስታወስ፤ በአመራር ቁርጠኝነትና ውሳኔ አሁን ላይ ነፍስ ዘርቷል ነው ያሉት፡፡

ፕሮጀክቱ ከኃይል ማመንጫነት ባለፈ ሌሎች በርካታ ትሩፋቶች እንደሚኖሩትም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም