ለሀገር ለሚያስፈልግ ነገር መትጋትና መከታተል ለውጤት እንደሚያበቃ የኮይሻ ግድብ ትልቅ ማሳያ ነው - ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ - ኢዜአ አማርኛ
ለሀገር ለሚያስፈልግ ነገር መትጋትና መከታተል ለውጤት እንደሚያበቃ የኮይሻ ግድብ ትልቅ ማሳያ ነው - ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ)፦ ለሀገር ለሚያስፈልግ ነገር መትጋትና መከታተል ለውጤት እንደሚያበቃ የኮይሻ ግድብ ትልቅ ማሳያ ነው ሲሉ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማን አስመልክቶ በኮይሻ ግድብ ከሚኒስትሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ለሀገር ለሚያስፈልግ ነገር መትጋትና መከታተል ለውጤት እንደሚያበቃ የኮይሻ ግድብ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
በኮይሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሀገራቸውን የሚወዱ ሰራተኞችን መመልከታቸውን በማውሳት ይህም ከስራ ዕድል ፈጠራ ባሻገር ለስልጠና አቅም መሆን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም እንደ ሀገር የተሻለ ስራ መሰራቱን የሚያሳይና የኮይሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ የፕሮጀክት ቅልጥፍና ውጤታማነት የታየበት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡