ቀጥታ፡

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አራት ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018 (ኢዜአ):- የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።

ቼልሲ ከሰንደርላንድ እና ኒውካስትል ዩናይትድ ከፉልሃም በተመሳሳይ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ዩናይትድ በኦልድራፎርድ ስታዲየም ብራይተንን ያስተናግዳል። 

ዩናይትድ በሩበን አሞሪም ስር በሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ለማግኘት ይጫወታል። 

ብሬንትፎርድ ከሊቨርፑል ምሽት 4 ሰዓት በጂቴክ ኮሙኒቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል ከሶስት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት እና ወደ ዋንጫ ፉክክር ለመመለስ የዛሬው ሶስት ነጥብ በእጅጉ  ይፈልገዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም