118ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
118ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ)፦ 118ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን "የማትደፈር ሀገር የማይበገር ሠራዊት" በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ ክንውኖች እየተከበረ ይገኛል፡፡
በአከባበሩ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ፣ ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች፣ የመከላከያ የክብር አባላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የሠራዊት አባላት መታደማቸውን የኢቢሲ ዘገባ ይጠቁማል።