ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን የተጠናቀቀውን የሳር ቤት-ጀርመን አደባባይ-ጋርመንት እና ፉሪ አካባቢ የኮሪደር ልማት ሥራ ገበኙ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን የተጠናቀቀውን የሳር ቤት-ጀርመን አደባባይ-ጋርመንት እና ፉሪ አካባቢ የኮሪደር ልማት ሥራ ገበኙ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን የተጠናቀቀውን የሳር ቤት-ጀርመን አደባባይ-ጋርመንት እና ፉሪ አካባቢ የኮሪደር ልማት ሥራ ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት 589 ሄክታር በላይ የሚሸፍነው ከባቢ ከካዛንቺስ ቀጥሎ ሰፊው የልማት ስፍራ ሆኗል ብለዋል።
ፕሮጀክቱ 16.5 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ፣ የ3 ኪሎ ሜትር ተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ብሎም 33 ኪሎ ሜትር የተዘረጋ የእግረኛ መንገድ ማካተቱንም ገልጸዋል።
የፕላዛዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የሕፃናት መጫወቻዎች እና 5.2 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራ መከናወኑንም እንዲሁ።
የመኪና ማቆሚያዎች፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል መሙያ ስፍራዎች፣ በግል እና የመንግሥት ተቋማት የተገቡ 1107 ሱቆች በልማት ሥራው የተሠሩ ናቸው።
የኮሪደር ልማቱ 50.5 ሄክታር አረንጓዴ ሥፍራ፣ የሕዝብ መጸዳጃዎች፣ 13.3 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መጋለቢያ መንገድ፣ 38 የአውቶቡስ እና ታክሲ መጫኛ-ማውረጃዎችንም አካትቷል።
እንደዚህ ያሉት ሀገራዊ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ሥራዎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ከማሳደግ ባሻገር የትራፊክ እንቅስቃሴን በማሻሻል፣ ማኅበራዊ መስተጋብርን በማጠንከር ደማቅ ለእንቅስቃሴ ምቹ እና ዘላቂነት ያላቸው የከተማ ሥፍራዎች በመፍጠር ረገድ ዐቢይ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ ነው ያሉት።