ቀጥታ፡

በሊጉ የዘጠነኛ ሳምንት የመክፈቻ  ጨዋታ ሊድስ ዩናይትድ ድል ቀንቶታል 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት ሊድስ ዩናይትድ ዌስትሃምን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በኢላንድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብሬንደን አሮንሰን እና ጆ ሮዶን የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ማቲያስ ፈርናንዴዝ ለዌስትሃም ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ሊድስ ዩናይትድ በ11 ነጥብ ደረጃውን ከ16ኛ ወደ 13ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉም ሶስተኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በአንጻሩ በሊጉ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ዌስትሃም በአራት ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም