በሊጉ መቀሌ 70 እንደርታ ከመቻል ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ያደረጓቸው ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል - ኢዜአ አማርኛ
በሊጉ መቀሌ 70 እንደርታ ከመቻል ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ያደረጓቸው ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 14/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው እየተካሄዱ ነው።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ ከመቻል ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
ኪቲካ ጅማ እና ፍጹም ዓለሙ ለመቀሌ 70 እንደርታ፣ አብዱልከሪም ወርቁ እና ቸርነት ጉግሳ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
በተያያዘም ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ምድረ ገነት ሽሬ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።