የጎንደር አብያተ መንግሥታት እድሳት የጎንደር ከተማን ወደ ሕይወት መልሷቷል - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ - ኢዜአ አማርኛ
የጎንደር አብያተ መንግሥታት እድሳት የጎንደር ከተማን ወደ ሕይወት መልሷቷል - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 14/2018(ኢዜአ)፡- የጎንደር አብያተ መንግሥታት እድሳት የጎንደር ከተማን ወደ ሕይወት መልሷቷል ሲሉ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።
ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የታሪካዊ ሥነ-ሕንፃዎች ጥበቃ እና እድሳት የሥነ-ሕንፃ እሴቶችን ለመጠበቅ ወሳኝ ነው ብለዋል።
ታላቅ የኢትዮጵያ ቤተ-መንግሥት የነበረው የጎንደር አብያተ መንግሥት በሚያምር እና የመነሻውን አርክቴክቸር በጠበቀ መልኩ ውብ ሆኖ መታደሱንም ገልጸዋል።
አሁን ጎንደር ድሮ እና ዘንድሮን አጣምራ የያዘች ማራኪ እና የምታምር ከተማ መሆኗን ነው ፕሬዚዳንቱ የጠቀሱት።