ቀጥታ፡

አርባምንጭ ከተማ እና ባህር ዳር ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 14/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት  ጨዋታ አርባ ምንጭ ከተማ እና ባህር ዳር ከተማ  ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። 

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ታምራት እያሱ በ75ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ አርባምንጭ ከተማ መምራት ችሏል።


 

በ90ኛው ደቂቃ ግርማ ዲሳሳ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል ለባህር ዳር ከተማ በባከኑ ደቂቃዎች ወሳኝ አንድ ነጥብ እንዲያገኝ አስችሎታል። 

በአሁኑ ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም  መቀሌ 70 እንደርታ ከመቻል ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል።

ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰዓት፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከምድረ ገነት ሽሬ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም