ቀጥታ፡

በዞኑ የልማት ስራዎችን ለማደናቀፍ በሚንቀሳቀሰው ጽንፈኛ ቡድን ላይ የተጠናከረ እርምጃ ይቀጥላል

ደሴ፤ጥቅምት 14/2018(ኢዜአ)፡-በደቡብ ወሎ ዞን የልማት ስራዎችን ለማደናቀፍና የሕዝብን ሰላም ለማናጋት በሚንቀሳቀሰው ጽንፈኛ ቡድን ላይ የተጠናከረ እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።

የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አሊ ይማም፥በዞኑ ያለውን ወቅታዊ የሰላም ሁኔታ በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በዞኑ የሰላምና ልማት ጉዳይ የሁሉም አጀንዳ ሆኖ እየተሰራበት መሆኑን አንስተዋል።

አሁን ላይ አስተማማኝ ሰላም መኖሩንና የልማት ስራዎችም ተጠናክረው መቀጠላቸውን ተናግረዋል።

የፅንፈኛ ቡድኑ የጥፋት ተላላኪዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች በስውር በመንቀሳቀስ ዘረፋና እገታ ለመፈፀም ሞክረው በሕዝቡ ትብብርና በጸጥታ ኃይሉ ጥብቅ ክትትል እርምጃ የተወሰደባቸው መሆኑን አስታውሰዋል።

በመሆኑም አሁን ላይ በዞኑ ሁሉም አካባቢዎች ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት በመፈጠሩ የልማት ስራዎችም ተጠናክረው መቀጠላቸውን አረጋግጠዋል።

የፅንፈኛው ቡድን ዓላማው መዝረፍና ሰዎችን ማገት መሆኑን ሕዝቡ በአግባቡ በመረዳቱ የሰላሙ ጠባቂ ሆኖ መቆሙን ተናግረዋል።

በዞኑ የልማት ስራዎችን ለማደናቀፍና የሕዝብን ሰላም ለማናጋት በሚንቀሳቀሰው ጽንፈኛ ቡድን ላይ የተጠናከረ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም