በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 14/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
አርባምንጭ ከተማ ከባህር ዳር ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት፣ ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መቀሌ 70 እንደርታ ከመቻል ከቀኑ 9 ሰዓት፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከምድረ ገነት ሽሬ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20 ክለቦች በሁለት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል። በእያንዳንዱ ምድብ 10 ክለቦች ይገኛሉ።
የምድብ አንድ ቡድኖች በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም፣ የምድብ ሁለት ቡድኖች በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተጫወቱ መሆኑን የሊጉ አክሲዮን ማህበር መረጃ ያመለክታል።