ቀጥታ፡

የጣና ፎረም ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ መካሄድ ይጀምራል

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 14/2018(ኢዜአ)፦አፍሪካውያን መሪዎችን እና ባለድርሻ አካላትን በአኅጉራዊ የሰላም እና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ በማወያየት ዘላቂ መፍትሔዎችን ለመቀየስ አልሞ የሚካሄደው 11ኛው የጣና የሰላም እና ደኅንነት መድረክ ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ መካሄድ ይጀምራል።


 

ዛሬ በሚጀምረው 11ኛው የጣና ፎረም ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ ሀገራት ልዑካን ትናንት ወደ ባሕርዳር መግባታቸው ይታወቃል።

እንዲሁም ነገ እና ከነገ በስቲያ ደግሞ ፎረሙ በአዲስ አበባ መካሄዱን እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም