ቀጥታ፡

ድሬዳዋ ከተማ የሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አሳክቷል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር  ድሬዳዋ ከተማ ወላይታ ድቻን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቤል ነጋሽ በ76ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቧን አስቆጥሯል።

ድሬዳዋ ከተማ በሊጉ የመጀመሪያው ሶስት ነጥቡን አግኝቷል።

በአንጻሩ ወላይታ ድቻ በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም