በሊጉ ፋሲል ከነማ ድል ሲቀናው ሸገር ከተማ እና አዳማ ከተማ አቻ ተለያይተዋል - ኢዜአ አማርኛ
በሊጉ ፋሲል ከነማ ድል ሲቀናው ሸገር ከተማ እና አዳማ ከተማ አቻ ተለያይተዋል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፋሲል ከነማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በረከት ግዛው እና አቤነዘር ዮሐንስ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ፋሲል ከነማ በሊጉ የመጀመሪያውን ድል አግኝቷል። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሸገር ከተማ እና አዳማ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
በአሁኑ ሰዓት ወላይታ ድቻ ከድሬዳዋ ከተማ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል።