ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አግኝቷል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አግኝቷል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ቡና አዲስ አዳጊውን ነጌሌ አርሲን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አቡበከር አዳሙ እና በፍቃዱ አለማየሁ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ገብረመስቀል ዱባለ ለነጌሌ አርሲ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ ቡናማዎቹ በሊጉ የመጀመሪያ ድላቸውን አሳክተዋል። በአንጻሩ ነጌሌ አርሲ በሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።