የ”DESSU” ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣንን ለመቋቋም ስምምነት ላይ ተደረሰ - ኢዜአ አማርኛ
የ”DESSU” ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣንን ለመቋቋም ስምምነት ላይ ተደረሰ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 13/2018(ኢዜአ)፦የ”DESSU” ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን የቴክኒክ ኮሚቴ እና የሚኒስትሮች ምክር ቤት መድረክ የ”DESSU” ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣንን ለማቋቋም በመስማማት ተጠናቋል።
የቴክኒክ ኮሚቴው እና የሚኒስትሮች ምክር ቤቱ መድረክ ጅቡቲን፣ ኢትዮጵያን፣ ደቡብ ሱዳንን እና ዩጋንዳን ያቀፈ ነው።
የ”DESSU” ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣንን ለመመስረት በጅቡቲ ከኦክቶበር 21-22/25 ለሁለት ቀናት ውይይት ሲያደርግ የቆየው የቴክኒክ ኮሚቴ እና የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮርደር አስተዳደር ባለስልጣን መቋቋም ላይ ተስማምቷል።
ከሁለት ሳምንት በኋላ በኢትዮጵያ በመገናኘት የአስተዳደሩን ሟቋቋሚያ ስምምነት ለመፈራረም በመግባባት እና የስምምነት ቃለ-ጉባኤ በመፈራረም ተጠናቋል።
የ”DESSU” ኮሪደር በአራቱ ሀገራት መካከል የውጪ ንግድ መንገዶችን በቀላሉ ለማገናኘት፣ መንገድ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎትን ለማሳለጥ ያለመ ነው።