ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በታንዛንያ ተሸንፏል 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12/2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በ16ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ ከታንዛንያ አቻው ጋር ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ የ2 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል።

በአዛም ኮምፕሌክስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አይሻ ጁማ እና ጃሚላ ራጃብ ለታንዛንያ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ሉሲዎቹ የመልስ ጨዋታቸውን ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ በመልሱ ጨዋታ ከሶስት እና ከዚያ በላይ ጎል በማስቆጠር ማሸነፍ ይጠበቅበታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም