የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የሲቪል ስራው ሥራው 70 ከመቶ ደርሷል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የሲቪል ስራው ሥራው 70 ከመቶ ደርሷል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12/2018 (ኢዜአ)፦ የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የሲቪል ሥራው አፈጻጸም 70 ከመቶ መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የ2018 ዓመተ ምህረት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በመጎብኘት ዛሬ መጀመሩን ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ ባለፈው ከነበራቸው ጉብኝት በኋላ የሚለካ የሥራ እድገት ታይቶበታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የግድቡ ከፍታ 128 ሜትር እና አጠቃላይ የሲቪል ሥራው 70 ከመቶ መድረሱን አመልክተዋል።
ይኽ ስኬት ለኃይል ምንጭ ዋስትናችን ላለን ያላሰለሰ ጽኑ ጥረት ምስክር የሚሆን ነው ብለዋል።