ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12/2018(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

በጉባኤው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።


 

በጉባኤው በቤተ ክርስቲያኒቱ አበይት ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ተገልጿል።

በዚሁ ወቅት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እንዳሉት ሠላምንና አንድነትን ለማጠናከር ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል።


 

የነገውን ትውልድ ልማታዊ ተስፋ እውን ለማድረግ ለዘላቂ ሰላም መስፈንና ለሀገር እድገት መረጋገጥ በአንድነትና በመግባባት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም