ቀጥታ፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ሶስት ወራት ውጤታማ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ተከናውነዋል - ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ጥቅምት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ሶሰት ወራት ውጤታማ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት መከናወናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን አስታወቁ።

የክልሉ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እየተገመገመ ነው።


 

በግምገማ መድረኩ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን እንደተናገሩት፤ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የትምህርት ንቅናቄ በስፋት የተከናወነበት፣ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትና የግብርና ስራ የተጠናከረበት ነው።

የሕብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመፍታት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአጭር ጊዜ ወደ ስራ እንዲገባ መደረጉንና በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት እየተሰጠ ነው ብለዋል።

በመጀመሪያ ሩብ ዓመት የማዕድን ዘርፉን ለማልማት እየተከናወነ ባለው ቅንጅታዊ ስራ 1ሺህ 709 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረጉን ጠቅሰዋል።

በመጀመሪያ ሩብ የበጀት ዓመት ለተከናወኑ ስራዎች ውጤታማነት ቅንጅታዊ አሰራር በመተግበሩ እንደሆነ ተናግረዋል።

የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ቃሲም ኢብራሂም እየቀረበ ሲሆን፤ በሪፖርቱ ላይ ጥልቅ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም