የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሹመት አፀደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሹመት አፀደቀ

ሐረር፤ ጥቅምት 12/2018 (ኢዜአ):-የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት አስቸኳይ ጉባዔ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሹመት አፀደቀ።
በአስቸኳይ ጉባዔው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፤ አቶ ሳላህዲን ቶፊቅን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ ለምክር ቤቱ በእጩነት አቅርበዋል።
በዚህም መሰረት ምክር ቤቱ በእጩነት የቀረቡትን አቶ ሳላህዲን ቶፊቅ፤ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሰሩ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል ።
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን የተሾሙት አቶ ሳላህዲን ቶፊቅ፤ በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።
የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት አስቸኳይ ጉባዔም ተጠናቋል።