በሩብ ዓመቱ በነዳጅ ማደያዎች ጥራትና ደኅንነቱ የተረጋገጠ ነዳጅ መቅረቡን አረጋግጠናል - ባለስልጣኑ - ኢዜአ አማርኛ
በሩብ ዓመቱ በነዳጅ ማደያዎች ጥራትና ደኅንነቱ የተረጋገጠ ነዳጅ መቅረቡን አረጋግጠናል - ባለስልጣኑ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12/2018(ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ ያለፉት ሶስት ወራት በነዳጅ ማደያዎች ላይ የነዳጅ ጥራትና ደኅንነት ክትትልና ቁጥጥር መደረጉን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ገለጸ።
በተደረገው ክትትልና ቁጥጥርም ጥራትና ደኅንነቱ የተረጋገጠ ነዳጅ መቅረቡን መረጋገጡን የባለስልጣኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ በቀለች ኩማ ለኢዜአ ተናግረዋል።
ባለፉት ሶስት ወራት 529ሺህ 526 ሜትሪክ ቶን ነጭ ናፍጣ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱንም ጨምረው አስታውቀዋል።
በተጨማሪም 141ሺህ 990 ሜትሪክ ቶን ቤንዚን ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱንም ነው የተናገሩት።
በጅቡቲ ተርሚናል የተራገፈው ነዳጅ ያለ ብክነትና ጉድለት ሙሉ በሙሉ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን ከጅቡቲ ሎዲንግ ሪፖርት ክትትል ማድረግ መቻሉንም አረጋግጠዋል።
በነዳጅ ማደያዎች ላይ የነዳጅ ጥራትና ደኅንነት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ጥራትና ደኅንነቱ የተረጋገጠ ነዳጅ ለተጠቃሚው መቅረቡን መረጋገጡንና ይህ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።