ባርሴሎና ኦሎምፒያኮስን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል - ኢዜአ አማርኛ
ባርሴሎና ኦሎምፒያኮስን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 11/2018(ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መርሃ ግብር ባርሴሎና ኦሎምፒያኮስን 6 ለ 1 ረቷል።
ማምሻውን በሉዊስ ካምፓኒስ ኦሊምፒክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፌርሚን ሎፔዝ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል።
ማርከስ ራሽፎርድ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ላሚን ያማል በፍጹም ቅጣት ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
አዩብ ኤልካቢ በፍጹም ቅጣት ምት ለኦሎምፒያኮስ ብቸኛዋን ጎል አስቆጥሯል።
የኦሎምፒያኮሱ ሳንቲያጎ ሄዜ በሁለት ቢጫ ካርድ በ57ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ተጫዋቹ ሁለተኛ ቢጫ ያየበት ጥፋት አወዛጋቢ ነበር።
የሄዜ መውጣት በቀሪው የጨዋታ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ልዩነት ፈጥሯል።
በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ካይራት አልማቲ እና ፓፎስ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።
የፓፎሱ ጆአኦ ኮሬያ በአራተኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።