ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር ያለመ የሁለትዮሽ ምክክር አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር ያለመ የሁለትዮሽ ምክክር አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 11/2018(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ዛሬ በሞስኮ ውይይት አድርገዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች የኢትዮጵያ እና ሩሲያን የረጅም ጊዜና ስትራቴጂካዊ አጋርነት የበለጠ ማጎልበት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በጥልቀት መክረዋል።
የሁለቱ ሀገራት የጋራ ትኩረቶች በሆኑ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይም ሀሳቦችን መለዋወጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በሩሲያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ሞስኮ መግባታቸው ይታወቃል።