ቀጥታ፡

ሴቶች የአካባቢያቸውን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ተሳትፎ ማጠናከር አለባቸው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 11/2018(ኢዜአ)፦በመዲናዋ ሴቶች ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት የአካባቢያቸውን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ተሳትፎ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው ሀገር በቀል የሰላምና መቻቻል እሴቶች በትውልድ ግንባታ ላይ ያላቸው ፋይዳና ከሴቶች የሚጠበቀውን ሚና አስመልክቶ ከሴት አደረጃጀቶች ጋር ውይይት አካሂዷል። 


 

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ሊዲያ ግርማ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት  ነው።

በከተማው ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ህዝቡን የሰላም ባለቤት ለማድረግ በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ሴቶች ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት የአካባቢያቸውን ሰላም ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ንቁ ተሳትፎ ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ሀይማኖታዊና የአደባባይ በዓላት እንዲሁም አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲካሄዱ ሴቶች ትልቅ ሚና መጫወታቸውን ተናግረዋል። 

በመድረኩ የተገኙት ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ በሰላም ጉዳይ ግንባር ቀደም በመሆን ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት መወጣታችንን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም