በባሌ ዞን የታየው ልማት የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬ መሆኑ የታየበት ነው - አቶ ሽመልስ አብዲሳ - ኢዜአ አማርኛ
በባሌ ዞን የታየው ልማት የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬ መሆኑ የታየበት ነው - አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 10/2018(ኢዜአ):- በባሌ ዞን የታየው ልማት የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬ መሆኑ የታየበት ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።
አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተረሳ እና የተደበቀ የነበረውን አካባቢ ከተደበቀበት ስላወጡልን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እናመሰግናለን ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በ‘የሶፍ ኡመር ወግ’ ከቀድሞ እና በሥራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ ላይ አቶ ሽመልስ አብዲሳ የባሌ ዞን በአጭር ጊዜ ተለውጦ በማየታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።
በባሌ ዞን የታየው ልማት የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬ መሆኑ የታየበት ነው ሲሉም ነው የተናገሩት።
የባሌ አካባቢ ባለመልማቱ ቁጭት እንደነበር ገልጸው አሁን ላይ በግብርና፤ በማዕድን፤ በቱሪዝም እና በከተማ ልማት ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንና ይህም ለኢትዮጵያ ትልቅ አቅም እንደሚሆን አንስተዋል፡፡
የባሌ አካባቢ የተረሳ እና የተደበቀ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሽመልስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቁርጠኝነት አካባቢው እንዲቀየር በማድረጋቸው ምስጋና አቅርበዋል።፡
ይህም ለሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ትልቅ መሰረት የሚሆንና በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች ጉልበት ይሆነናል ብለዋል።