ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለምታደርገው ጥረት ሩሲያ ሙሉ ድጋፍ እንደምትሰጥ ገለጸች

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 10/2018(ኢዜአ)፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ከሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲሞ ሬሽንኮቭ ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን አድማሰ ሰፊ እና የቆየ ትብብር የበለጠ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በዚሁ ወቅትም ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለምታደርገው ጥረት ሩሲያ ሙሉ ድጋፍ እንደምትሰጥ ሚኒስትር ማክሲሞ ሬሽንኮቭ አረጋግጠዋል።

በተመሳሳይ ከሩሲያ አቶሚክ ኤጄንሲ እና ሌሎች ባለሥልጣናት ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያይተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ሞስኮ ገብተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም