የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ የአስክሬን ሽኝት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተገኙበት በሚሊኒዬም አዳራሽ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ የአስክሬን ሽኝት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተገኙበት በሚሊኒዬም አዳራሽ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 10/2018 (ኢዜአ)፦የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ የአስክሬን ሽኝት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተገኙበት በሚሊኒዬም አዳራሽ እየተካሄደ ነው።
በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ በሚገኘው የሽኝት መርሃ-ግብር ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴን ጨምሮ፣የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፣ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ፣የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማሕበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች፣የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም በርካታ የሙስሊም ማህበረሰብ ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ አስክሬን ፒያሳ በሚገኘው ኑር መስጂድ የዱዓ እና የሽኝት ሥነ-ሥርዓት መካሄዱ ይታወቃል።
የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ አስክሬን ለ40 ዓመታት ባስተማሩበት ኑር መስጂድም ሶላተል ጀናዛ ተሰግዶበታል።
በሚሊኒዬም አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘው የአስክሬን ሽኝት ሲጠናቀቅም ሥርዓተ ቀብራቸው የሚፈፀም ይሆናል።