ኢትዮጵያ መድን እና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ መድን እና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 10 /2018 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ መድን እና አዳማ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ዛሬ ከቀትር በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የአዳማ ከተማው ሃይደር ሸረፋ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
ሃይደር አምና በአምበልነት ኢትዮጵያ መድንን እየመራ የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱ የሚታወስ ሲሆን ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጦም ነበር።
ኢትዮጵያ መድን የዋንጫ ክብሩን የማስጠበቅ ጉዞውን ነጥብ በመጣል ጀምሯል።
በሌሎች የአንደኛ ሳምንት መርሃ ግብሮች ባህር ዳር ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና በአዲስ አበባ ስታዲየም፣ ምድረ ገነት ሽሬ ከመቀሌ 70 እንደርታ ጋር በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተመሳሳይ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።