ቀጥታ፡

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስክሬን ፒያሳ በሚገኘው ኑር መስጂድ የዱዓ እና የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 10/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስክሬን ፒያሳ በሚገኘው ኑር መስጂድ የዱዓ እና የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።


 

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን ለ40 ዓመታት ባስተማሩበት ኑር መስጂድ ሶላተል ጀናዛ ተሰግዶበታል።

በአሁኑ ወቅት አስክሬናቸው ወደ ሚሌኒየም አዳራሽ እየተሸኘ ሲሆን ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የክብር ሽኝት ከተረገላቸው በኋላ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ሥርዓተ ቀብራቸው የሚፈፀም ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም