ኢትዮጵያ መድን የዋንጫ ክብሩን የማስጠበቅ ጉዞውን ከአዳማ ከተማ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ይጀምራል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ መድን የዋንጫ ክብሩን የማስጠበቅ ጉዞውን ከአዳማ ከተማ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ይጀምራል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 10 /2018 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ውሎ ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ከነዚህ መርሃ ግብሮች መካከል አዳማ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ የሚያደርጉት ጨዋታ ይገኝበታል።
ኢትዮጵያ መድን በ2017 ዓ.ም የውድድር ዓመት በ73 ነጥብ የሊጉን ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንሳቱ ይታወቃል።
ተጋጣሚው አዳማ ከተማ አምና በሊጉ በ39 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
መድን የዋንጫ ክብሩን አስጠብቆ ለመቆየት የሚያደርገውን ጉዞ ዛሬ ይጀምራል።
በአንጻሩ አዳማ ከተማ ባለፈው የውድድር ዓመት ከነበረው ደካማ አቋም የተሻለ እንቅስቃሴ ለማድረግ ይጫወታል።
ቡድኖቹ በ2017 ዓ.ም በሊጉ ሁለት ጊዜ ተገናኝተው ኢትዮጵያ መድን ሁለቱንም ጨዋታዎች ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
በሌላኛው መርሃ ግብር ባህር ዳር ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ምድረገነት ሽሬ ከመቀሌ 70 እንደርታ ከቀኑ 10 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታል።