ቀጥታ፡

የሰላም ሚኒስቴር በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ ሕልፈት የተሰማውን ሐዘን ገለጸ

አዲስ አበባ ፤ጥቅምት 9 / 2018 (ኢዜአ)፦ የሠላም ሚኒስቴር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕረዝዳንት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ በማረፋቸው የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን ገለጸ። 

ሚኒስቴሩ  ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ኢድሪስ በአመራር ዘመናቸው የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አንድነት እንዲጠናከር እና ተቋሙ በሕግ ዕውቅና አግኝቶ እንዲቋቋም ባደረጉት በጎ አስተዋጽዖ  ይታወሳሉ ብሏል።

የሠላም ሚኒስቴር  ለሀገራችን ሰላምና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት መጎልበት በቅንነት ያደረጉት አስተዋፅዖ ሁሌም የሚዘከር ነው ያለው።

ሚኒስቴር መ/ቤቱ ለቤተሰባቸው፣ ለሃይማኖቱ ተከታዮችና ለመላው የሀገራችን ሕዝቦች መጽናናቱን ተመኝቷል።

#Ethiopian_News_Agency 
#ኢዜአ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም