ቀጥታ፡

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

አዲስ አበባ ፤ጥቅምት 9 / 2018 (ኢዜአ) ፦ፕሬዚዳንት  ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።  

ፕሬዚዳንቱ ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት በነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ እረፍት በጥልቅ አዝኛለሁ ብለዋል፡፡

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በመልካም አበርክቷቸው ሁሌም የሚታወሱ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው ኢትዮጵያውያን መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

#Ethiopian_News_Agency  #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም