መቻል የውድድር ዓመቱን በድል ጀምሯል - ኢዜአ አማርኛ
መቻል የውድድር ዓመቱን በድል ጀምሯል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 8/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ መቻል ወላይታ ድቻን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ መናፍ ኢሞሮ በ92ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል በማስቆጠር ለቡድኑ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አስገኝቷል።
ዛሬ በፕሪሚየር ሊጉ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 በማሸነፍ የደርቢ ድል ተቀዳጅቷል።
ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።