ቀጥታ፡

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት :-

በሕዝበ ሙስሊሙ ማህበርሰብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸው ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በማረፋቸው ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል።

ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በዲን ያበረከቱት አስተዋጽዖ ላቅ ያለ ነው፡፡ ለህዝበ ሙስሊሙ ሁለንተናዊ ጥቅም የሰሩና ለችግሮችም እራሳቸውን የመፍትሔ አካል አድርገው ጽናትን ያሳዩ ታላቅ ሰው ነበሩ፡፡

ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑር።

ለመላው ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመድና ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መጽናናትን እመኛለሁ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም