ቀጥታ፡

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በባሌ ዞን በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች እና አቅመ ደካማ እናቶች 6000 ጫማዎችን ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 9/2018(ኢዜአ)፦ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በባሌ ዞን በነበራቸው ጉብኝት በዞኑ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች እና አቅመ ደካማ እናቶች 6000 ጫማዎችን ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው አበይት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ ሲሆን በትምህርት ዘርፉ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ በመተግበር ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን በመፍጠር ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡


 

ይህንን ሚና በማጠናከር ላለፉት አምስት አመታት በመላው የሀገራችን ክፍሎች ጽህፈት ቤቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ከመገንባት በተጨማሪ ለተገነቡት እና በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ተማሪዎች ያለማቋረጥ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ ሲሆን የዛሬው ስጦታም የዚህ ሥራ አንዱ አካል እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም