ቀጥታ፡

በተጠባቂው የሊግ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 8/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ብሪያን ምቡዌሞ እና ሃሪ ማጓየር የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ኮዲ ጋፕኮ ለሊቨርፑል ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። 

ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን ያስተናገደው የወቅቱ የዋንጫ ባለቤት ሊቨርፑል በ15 ነጥብ ከሁለተኛ ወደ አራተኛ ዝቅ ብሏል። ከሊጉ አርሰናል ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ከፍ ብሏል።

ማንችስተር ዩናይትድ በ13 ነጥብ ደረጃውን ከ11ኛ ወደ 9ኛ ከፍ አድርጓል።

ዩናይትድ በሩበን አሞሪም ስር በሊጉ ተከታታይ ድሉን ለመጀመሪያ ጊዜ አስመዝግቧል።

ቀን ላይ በተደረገ ሌላኛው ጨዋታ አስቶንቪላ ቶተንሃም ሆትስፐርስን 2 ለ 1 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም