ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 9/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ መልዕክት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በማረፋቸው ኀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል።

ሐጂ ዑመር በአመራር ዘመናቸው የተለያዩ ወገኖች ወደ አንድነት እንዲመጡ እና የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሕግ ዕውቅና እንዲኖረው ያደረጉትን አስተዋጽዖ ሁሌም እናስታውሰዋለን ሲሉም ገልጸዋል።

ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች መጽናናትን እመኛለሁ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀዘን መግለጫ መልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም