ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ - ኢዜአ አማርኛ
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 9/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ኢቢሲ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዝደንቱ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን ይመኛል።